የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ የመከፈቻ ሥነ ሥርዓትና ጅማሮ

የኦሎምፒክ ውድድሮችን እንደምን መመልከት እንደሚችሉ፣ ሙሉ የውድድር ሰንጠረዥና የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ተሳትፎዎች

Paris 2024.png

The opening ceremony for the 2024 Paris Olympics will be held on Friday, 26 July. Credit: Getty / Kevin Voigt

የበጋ ኦሎምፒክ ትናንት ጁላይ 26 / ሐምሌ 19 በፓሪስ ከተማ ቀልብ በሚሰርቅ ልዩ ዝንቅ ዝግጅቱ አስደማሚና "በመጨረሻው እራት" አቅርቦቱ በክርስትና እምነት መሪዎች ዘንድ አነጋጋሪ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓትነት ተጀምሯል።

የኦሎምፒክ ዋነኛ ነበልባል በቴዲ ራይነርና ሜሪ-ሆዜ ፐርክ ተለኩሷል።
gettyimages-2162986145-612x612.jpg
PARIS, FRANCE - JULY 26: Torchbearers Teddy Riner (R) and Marie-Jose Perec light up the Olympic cauldron during the opening ceremony of the Paris 2024 Olympic Games in Paris, France, July 26, 2024. Credit: Pool/Getty Images)
መጠናቀቂያውና የመዝጊያ ሥነ ሥርዓቱ እሑድ ኦገስት 11 / ነሐሴ 5 ይሆናል።

በሁለት ሳምንቱ የኦሎምፒክ ውድድር 10,714 አትሌቶች በ32 የስፖርት ዘርፎች፤ በ329 ክንውኖች ተሳታፊዎች ይሆናሉ።
gettyimages-2163831487-612x612.jpg
PARIS, FRANCE - JULY 26: Athletes from Team Australia are seen on a boat on the River Seine during the opening ceremony of the Olympic Games Paris 2024 on July 26, 2024 in Paris, France. Credit: Maja Hitij/Getty Images
የስደተኛ ኦሎምፒክ ተሳታፊዎችን አክሎ፣ አውስትራሊያና ኢትዮጵያን ጨምሮ 206 ሀገራት ለወርቅ፣ ብርና ነሐስ ሜዳሎች ባለቤትነት ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ።
gettyimages-2162934860-612x612.jpg
PARIS, FRANCE - JULY 26: Athletes from Ethiopia's delegation sail in a boat along the river Seine at the start of the opening ceremony of the Paris 2024 Olympic Games in Paris on July 26, 2024. Credit: Anadolu/Anadolu via Getty Images
ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ መድረክ

ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችው በሜልበርን ኦሎምፒክ እ.አ.አ1956 ሲሆን ከዚያን ጊዜ አንስቶ በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት 1976 (ሞንትሪያል) 1984 (ሎስ አንጀለስ) እና 1988 (ሶል) በስተቀር እስካሁኑ የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ድረስ ተሳትፋለች።

ኢትዮጵያ ከተሳተፈችባቸው የኦሎምፒክ ውድድር 23 ወርቅ፣ 12 ብርና 23 ነሐስ፤ በጥቅሉ 58 ሜዳሎችን አግኝታለች።

ኢትዮጵያ ሁሉንም የኦሎምፒክ ሜዳሎች ያገኘችው በአትሌቲክስ ውድድር ነው።

ከ58ቱ ሜዳሎች ውስጥ ከአንድ በላይ የኦሎምፒክ ሜዳል ያገኙ አትሌቶች 11 ናቸው።

  • ጥሩነሽ ዲባባ (2004 - 2016) 3 ወርቅና 3 ነሐስ በድምሩ 6 ሜዳሎችን በማግኘት በቀዳሚ ሥፍራ ላይ ስትገኝ፤
  • ስለሺ ስህን 2 ብር (2004 - 2008) በማግኘት 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ከአንጋፋዎቹ፤

  • ማሞ ወልዴ፤ 1 ወርቅ፣ 1 ብርና 1 ነሐስ (1968 - 1972) በድምሩ 3 በማግኘት 6ኛ ደረጃ፤
  • አበበ ቢቂላ፤ 2 የወርቅ ሜዳል (1960 - 1964) በማግኘት 8ኛ ደረጃ ይዘው ይገኛሉ።
አውስትራሊያ በኦሎምፒክ መድረክ

አውስትራሊያ ዘመናዊ ኦሎምፒክ ከተጀመረ 1986 አንስቶ በእያንዳንዱ የኦሎፒክ 29 መድረክ የተሳተፈች ሲሆን፤ 167 ወርቅ፣ 177 ብርና 213 ነሐስ፤ በጥቅሉ 517 ሜዳሎችን አሸንፋለች።

ሙሉ የኦሎምፒክ ውድድር ሰንጠረዥ

ሙሉ የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ውድድሩን

እንደምን መመልከት እንደሚችሉ

የአውስትራሊያ 9 ኔትዎርክ የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ የቴሌቪዥን ስርጭት መብቶችን አለው።

ቻናል 9 ከዜናና የብሔራዊ ራግቢ ሊግ ጨዋታዎች በስተቀር ከመክፈቻ ሥነ ሥርዓት እስከ መዝጊያ ሥነ ሥርዓት ድረስ በቀን ለ22 ሰዓታት ያሰራጫል።

9Gem የኦሎምፒክ ክንውኖችን እስከ ኦገስት 12 / ነሐሴ 6 ድረስ በቀን ለ24 ሰዓታት ያስተላልፋል።

Share
Published 27 July 2024 3:56pm
Updated 27 July 2024 4:01pm
By Kassahun Seboqa Negewo, NACA
Source: SBS

Share this with family and friends