ገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን ባደረበት ሕመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ነቢይ ባደረበት ሕመም ሕክምና ሲከታተል ቆይቶ፤ ድንገት ያረፈው ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ረፋዱ ላይ ነው።

mekonnen.png

Author and Poet Nebiy Mekonnen. Credit: Supplied

የአዲስ አድማስ ዝግጅት ክፍል፣ የጋዜጣው መሥራችና ዋና አዘጋጅ የነበረው ገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን ሕይወት ማለፉን ልጁ ራዕይ ነቢይ ገልጧል።

ከአዲስ አድማስ መሥራቾች አንዱ የሆነውና በዋና አዘጋጅነት ጋዜጣዋን በመምራት ተወዳጅ ካደረጓት በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ነቢይ ብርቱ ተርጓሚ፣ ገጣሚና ወግ አዋቂ የጥበብ ሰው በመሆኑ ይታወቃል።
admas.jpg
ነቢይ በደርግ ዘመን በእስር ላይ እያለ Gone with the wind የተሰኘውን የማርጋሬት ሚቼል መፅሀፍ በሲጋራ ወረቀት ላይ ወደ አማርኛ እንደተረጎመም ይነገርለታል።

ነቢይ የፃፋቸው ግጥሞች ወደ እንግሊዝኛ እና ፈረንሳይኛ የተተረጎሙ ሲሆን፤ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በተከታታይ ይፅፋቸው በነበሩ "የኛ ሰው በአሜሪካ" የተሰኘው የጉዞ ማስታወሻ ተወዳጅነትን አትርፎለታል።

ነቢይ ሕይወቱ ያለፈው በተወለደ በ68 ዓመቱ ሲሆን የሶስት ሴት ልጆች አባት ነበር። የቀብሩ ሥነ ሥርዓት ባለቤቱ እና ልጁ ከውጭ ሀገር ከመጡ በኋላ እንደሚፈፀም ሸገር ኤፍኤም 102·1 አስደምጧል።


Share
Published 4 July 2024 7:58am
Updated 4 July 2024 8:06am
By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends