ማኅበሩ፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴርና ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚያካሂዱት ዘመቻ ከዳኝነት ነፃነትና ከሕግ የበላይነት መርህ ያፈነገጠና ዳኞች ሕግን መሠረት አድርገው "በነፃነት እንዳይሠሩ ያልተገባ ጫና" እንደሚፈጥር ገልጧል።
በአገሪቱ ሕግ በወንጀልም ኾነ በፍትሐብሄር የተፈረደበት ወገን ይግባኝ የመጠየቅ ሕገመንግሥታዊ መብት እንዳለው የጠቀሰው ማኅበሩ፣ ግለሰቡ ይግባኝ ማቅረብ የለበትም የሚል ዘመቻ ማድረግ "በሕግ የመዳኘት መብትን አደጋ ላይ የሚጥል" እና በፍርድ ቤቱ ላይ "ያልተገባ ጫና በማሳደር የዜጎችን ፍትሕ የማግኘት መብት" ይጥሳል ብሏል።
ሚንስቴሩ ይግባኝ መቅረቡን ተቃውሞ በጉዳዩ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚሠራ መግለጡ ይታወሳል።